Fana: At a Speed of Life!

ቢሮው ህዝብን በማሳተፍ የክልሉን ዘላቂ ሰላም እናረጋግጣለን አለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ህዝቡን በባለቤትነት በማሳተፍና በማቀናጀት በክልሉ ቀጣይነት ያለው ሰላም ለማረጋገጥ እንደሚሰራ የሐረሪ ክልል ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ገለጸ።

ሃላፊው አቶ ጥላሁን ዋደራ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ ህዝቡ ካለምንም ስጋት በሰላም ወጥቶ እንዲገባ እና ፊቱን ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ እንዲያተኩር  ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ አበረታች የፀጥታ ስራዎችን በማጠናከር እና ክፍተቶችን በማረም የክልሉ ሰላም እንዲጎለብት ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል።

ለዚህም ህዝቡን  በባለቤትነት በማሳተፍና በማቀናጀት በክልሉ ቀጣይነት ያለው ሰላም እንዲረጋገጥ እንደሚሰራ ነው የገለጹት።

ከቀድሞው የቢሮ ሃላፊ አቶ ናስር ዩያ ርክክብ በማድረግ ከቢሮው የማኔጅመንት አባላት ጋር ትውውቅና ውይይት ማድረጋቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ሰላም ወዳዱ የክልሉ ህዝብም በአካባቢው ሰላም እንዲጠናከር በሚከናወኑ ተግባራት ድጋፉን እንዲቀጥልም  ጠይቀዋል፡፡

አሸባሪው የህወሃት ቡድን ግብዓተ መሬት እስከፈፀም ድረስም የክልሉ የፀጥታ አካላትና ወጣቶች እያደረጉት ያለው አስተዋፅኦ አጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.