Fana: At a Speed of Life!

የሰው ልጆች እና የአየር ንብረት ለውጥ ለካርበን ልቀት መጨመር ምክንያት ሆነዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለማችን የሚገኙ 10 ጥብቅ ደኖች በሰው ልጆች ድርጊት እና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ላለፉት 20 ዓመታት በደረሰባቸው ተጽዕኖ ወደ ካርበን አመንጪነት መቀየራቸውን ሪፖርት አመላከተ።
የተባበሩት መንግስታት የሣይንስ፣ የባሕልና የትምህርት ድርጅት (ዩኔስኮ) እና የተለያዩ በተፈጥሮ ሐብቶች ላይ የሚሰሩ ተቋማት ለ20 አመታት ያደረጉትን ጥናት ይፋ አድርገዋል።
በጥናታቸውም የሰው ልጆች ድርጊት፤ ጥብቅ ደኖችን መመንጠር፣ የደን መጨፍጨፍ እና በተለያዩ ጊዜያት ደን ላይ የሚደርሱ የሰደድ እሳት አደጋዎች እየከፋ ለመጣው የካርበን ልቀት መጠን መጨመር በዋና ምክንያትነት ጠቅሰዋል።
ከዚህ ባለፈም የአየር ንብረት ለውጥ ለካርበን ልቀት መጠኑ መባባስ ሌላኛው ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል።
በዚህ ረገድም በጥብቅ ደኖች ላይ በተለያየ ምክንያት በሚከሰተው ሰደድ እሳት እና ቃጠሎ የሚፈጠረው ጭስ ለካርበን ልቀቱ መጨመር ምክንያት መሆኑንም በጥናታቸው አመላክተዋል።
በዚህ መልኩ ጉዳት ከደረሰባቸውና ለካርበን ልቀቱ መባባስ የበኩላቸውን አበርክተዋል ከተባሉ የዓለም ቅርስ ደኖች መካከል የሱማትራ ደን፣ በማሌዢያ የሚገኘው የኪናባሉ ፓርክ እንዲሁም በአውስትራሊያ የሚገኙት ተራሮች ተጠቅሰዋል።
በአሜሪካ የሚገኙት ዮሴማይት እና ግራንድ ካኒየን ፓርክም ለካርበን ልቀት መጨመር የበኩላቸውን ሚና ተጫውተዋል ነው የተባለው።
ጥናቱ የሳተላይት ካርታ በመጠቀም ከፈረንጆቹ 2001 እስከ 2020 ድረስ በዓለም ቅርስ ደኖቹ ውስጥ የታመቀውን እና የተለቀቀውን የካርበን ልቀት መጠን በመመዝገብ የተሰራ መሆኑን አልጀዚራ በዘገባው አመላክቷል።
የሰው ልጆች ድርጊትና የአየር ንብረት ለውጥ የካርበን ልቀት እንዲጨምር ከማድረጉም ባለፈ በደኖች ውስጥ ይገኙ የነበሩ ወደ 180 የሚደርሱ የዛፍ ዝርያዎች እንዲጠፉና የደን ሽፋንም በከፍተኛ ሁኔታ እንዲመናመን አድርጓል።
ከዚህ ባለፈም በእርሻ ስራ እና የግብርና ምርቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳትን ሲያስከትል፥ ለሚስተዋለው ሙቀት መጨመርም ምክንያት ሆኗል ነው የተባለው፡፡ ብራዚል፣ ኢንዶኔዥያ፣ ማሌዢያ፣ ቻይና፣ ኮሎምቢያ እና ቬኒዝዌላ ደግሞ የዚህ ጉዳት ሰለባዎች መሆናቸው በጥናቱ ተጠቅሷል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
6
Engagements
Boost Post
6
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.