የበለጸገች ኢትዮጵያን ለማየት የሚዲያ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም የልማትና የዴሞክራሲ ትልሞችን እውን በማድረግ የበለጸገች ኢትዮጵያን እንድናይ የሚዲያ ሚና ከፍተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ገለጸ፡፡
ቢሮው ከሚዲያ አካላት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የውውይት መድረክ እያካሄደ ነው።
ቢሮው በከተማ አስተዳደሩ እንደ አዲስ ከተደራጀ በኋላ ከተማ አስተዳደሩ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በሌሎች ጉዳዮች የተደራጀ መረጃን ለማቅረብ መዘጋጀቱን ገልጿል።
በዚህም በእውቀት፣ በእውነት እና በመረጃ የተደገፈ ሳምንታዊ መግለጫን ጨምሮ በተሳለጠ መልኩ እስከ ወረዳና ቀበሌ የወረደ ወጥ እና ፈጣን የኮሙዩኒኬሽን ስራ እንደሚሰራም ነው የገለጸው።
በከተማዋ የሚታዩ አላስፈላጊ እና ሃገርን እና ማህበረሰብን የማይመጥኑ የማስታወቂያ ስራዎችን በመቆጣጠር እርምጃ እንደሚወስድም አስታውቋል።
ከዚህ ባለፈም በተለያዩ አደረጃጀቶች እራሱን በማጠናከር ከተማዋን ብሎም ሃገርን በሚመለከቱ ወቅታዊ እና ዘላቂ ጉዳዮችን ላይ ከሚዲያው ጋር ተቀራርቦ እንደሚሰራም በመድረኩ ተነስቷል።
በፍሬህይወት ሰፊው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!