የሀገር ውስጥ ዜና

የኤፌሶን-መሀልሜዳ መንገድ ግንባታ 95 በመቶ ተጠናቀቀ

By Meseret Awoke

October 28, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቀምት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 61 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የኤፌሶን-መሀልሜዳ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በተያዘው በጀት ዓመት ሙሉ ለሙሉ እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታውቋል።

ለግንባታው ስራው የተመደበው 1 ቢሊየን 352 ሚሊየን ብር በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን መሆኑንም ባለስልጣኑ ገልጿል።

የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ በስፋት የአፈር ጥንካሬን መጨመር በሚያስችል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ግንባታው የተከናወነ ሲሆን÷ ይህም የመሬት መንሸራተትን በከፍተኛ ሁኔታ ለመከላከል የሚያግዝ መሆኑንም ባለስልጣኑ አስታውቋል።

መንገዱ የኤፌሶን ከተማን ከመሀል ሜዳ ከተማ ጋር በማስተሳሰር፥ በኤፍራታ ግድም ወረዳ እና በመንዝ ወረዳዎች የሚመረቱ የተለያዩ የግብርና ምርቶችን ለገበያ ለማቅረብ የጎላ ሚናን ያበረክታል ተብሏል ።

ከዚህ ባለፈም በአካባቢው ለሚገኘው ለጎጎ ጥብቅ የማህበረሰብ ፓርክ የጎብኚ ፍሰት ለመጨመር እና የመንገድ ትስስርን ለማሳደግ ይረዳል መባሉን የባለስልጣኑ መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!