Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል 131 ሺህ 67 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ -የክልሉ ትምህርት ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልሉ ትምህርት ቢሮ የ2013 የ12ኛ ክፍል ፈተና በተሳካ ሁኔታ መካሄድ በሚችልበት ሁኔታ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ማተብ ታፈረ ፥ውይይቱ ባለድርሻ አካላት በተለያዩ ምክንያቶች የዘገየው ፈተና በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጨማሪ አቅም መፍጠር ይችላል ብለዋል።
በህልውና ዘመቻ ውስጥ የሚካሄደው የዘንድሮ ፈተና እንከን እንዳይገጥመው ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረጋል ያሉት ሀላፊው፥ ለተግባሩ መሳካት በቂ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀዋል።
በክልሉ 154 ሺህ 447 መደበኛ 9 ሺህ 560 የግል ተፈታኞች በድምሩ 164 ሺህ 107 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ መሆናቸውን የተናገሩት የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ ሙላው አበበ ፥ 131 ሺህ 67 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ነው ያሉት።
በክልሉ የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች በሰሜን ጎንደር 2 ትምህርት ቤቶች ደቡብ ወሎ 45 እንዲሁም ደሴ ከተማ 3 ትምህርት ቤትች ፈተና አይሰጥባቸውም ያሉት ምክትል ቢሮ ሀላፊው፥ 32 ሺህ 940 የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናውን አይወስዱም ተብሏል።
ፈተናው ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲሰጥ የፀጥታ አካላት ተገቢውን ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፥ ለተግባራዊነቱም በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው ተገልጿል።
ውይይቱ አሁንም በባህርዳር ከተማ እንደቀጠለ ነው።
በሰላም አስመላሽ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
100
Engagements
Boost Post
94
3 Comments
3 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.