Fana: At a Speed of Life!

የሱዳን አለመረጋጋት ከኢትዮጵያ ባለፈ ለቀጠናው አይበጅም – የፖለቲካ ተንታኞች

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 18 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን አለመረጋጋት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር የፖለቲካ ተንታኞች ገለጹ።
የኢትዮጵያ የሠላምና ልማት ማዕከል ምክትል ሊቀ-መንበር ኡስታዝ ጀማል በሽር እና በኢትዮጵያ እና አረብ ሃገራት ግንኙነት ላይ ተመራማሪ ዛሂድ ዛይዳን ከሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ የሠላምና ልማት ማዕከል ምክትል ሊቀ-መንበር ኡስታዝ ጀማል በሽር፥ በሱዳን ያለው አለመረጋጋት ኢትዮጵያ ካላት መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ አንጻር ተፅዕኖ እንደሚፈጥርባት ተናግረዋል።
እንድ ምክትል ሊቀ መንበሩ ገለጻ የግብፅ ሚዲያ ተቋማት “ኢትዮጵያ በሱዳን በተከሰተው አለመረጋጋትና ውጥረት ደስተኛ ናት” በሚል እየዘገቡ ነው።
ይልቁንም ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2018 በሱዳን ተከስቶ የነበረውን ፖለቲካዊ ውጥረት በማረጋጋት ከሲቪሉና ወታደራዊ ክፍል የተውጣጣ ጥምር መንግስት እንዲመሰረት ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ሚና መወጣቷን አስታውሰዋል።
ከጥምር መንግስት ምስረታው ባለፈም የሽግግር ጊዜ ህገ መንግስት እንዲዘጋጅ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱንም ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያ እና አረብ ሃገራት ግንኙነት ላይ ተመራማሪ የሆኑት ዛሂድ ዛይዳን በበኩላቸው፥ በሱዳን ያለው ፀጥታ እና መረጋጋት የኢትዮጵያ መረጋጋትና ደህንነት አካል መሆኑን አንስተዋል።
ሃገራቱ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው ያሉት ተመራማሪው፥ በሱዳን ያለው አለመረጋጋት ኢትዮጵያ ላይ ብቻ ሳይሆን ምስራቅ አፍሪካ ላይም ተፅዕኖው የጎላ መሆኑን አስምረውበታል።
አያይዘውም የውጭ ሃይሎች በሱዳን የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባት እንደሌለባቸውም አጽንኦት ሰጥተዋል።
መንግስት በሳምንቱ ባወጣው መግለጫ የሱዳንን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን መግለጹ ይታወሳል።
በመግለጫው የሱዳናውያንን እና የሃገሪቱን ሉዓላዊነት ማክበር እንደሚገባ እና በሱዳን የውስጥ ጉዳይ የሚደረግ የውጭ ሃገራት ጣልቃ ገብነት አግባብ አለመሆኑን ማንሳቱም የሚታወስ ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 2 people
0
People reached
0
Engagements
Distribution Score
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.