Fana: At a Speed of Life!

የሃይማኖት ተቋማት ትውልድን በስነ-ምግባር በሚያንፁ ተግባራት ላይ ሊያተኩሩ ይገባል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃይማኖት ተቋማት ትውልድን በስነ-ምግባር በሚያንፁና አንድነትን በሚያጠናክሩ ተግባራት ላይ አተኩረው መስራት እንዳለባቸዉ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስገነዘበ።

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ባካሄደው 10ኛ ጠቅላላ መደበኛ ስብሰባ በ2013 የእቅድ አፈፃፀምና የሂሳብ ኦዲት ሪፖርት እንዲሁም የ2014 በጀት ዓመት እቅድ ላይ መክሯል።

የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስና የጉባኤው የቦርድ ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ መልከጸዲቅ ÷ የሃይማኖት ተቋማት ስለ ኢትዮጵያ ሠላም በመስበክ መልዕክቶችን በአደባባይ ጭምር ሲያስተላልፉ መቆየታቸውን ጠቅሰዋል።

ባለፈው ዓመት በተለይም በሠላም እሴት ግንባታ፣ በስነ-ምግባርና የሞራል ግንባታ ላይ በማተኮር ውይይቶችና ስልጠናዎች መካሄዳቸውን ተናግረዋል።

ሀገርን ማልማት ለመንግስት ብቻ የሚተው ባለመሆኑ ቤተ-እምነቶች በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብርና ሌሎች የልማት ስራዎች ላይ መሳተፋቸውንም አውስተዋል።

የሃይማኖት ተቋማቱ በቀጣይም አንድነትን በሚያጠናክሩና ትውልድን በስነ-ምግባር በሚያንፁ እንዲሁም የሀገርን ልማት በሚያጠናክሩ ስራዎች ላይ ማተኮር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.