የሀገር ውስጥ ዜና

ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጅግጅጋ ገቡ

By Meseret Awoke

October 28, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራውና የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሚኒስትር ዴኤታዎችና ሌሎች ባለሙያዎችን ያካተተው ልዑክ ዛሬ ጅግጅጋ ገብቷል።

ልዑኩ ጅግጅጋ ሲገባ የሶማሊ ክልል ምክትል ፕሬዚደንት አቶ ኢብራሂም ኡስማን፣ የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ሀላፊ ዶክተር ሁሴን ሄሺና ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ የስራ ሀላፊዎች ለልዑኩ ደማቅ አቀባበል አድርጓል።

ልዑኩ ነገ በጅግጅጋ ከተማ የሚጀመረው አመታዊው የጤና ዘርፍ የምክክር ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፍ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!