Fana: At a Speed of Life!

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ያስመርቃል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለ66ኛ ጊዜ ከ4 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ነገ እንደሚያስመርቅ ተገለጸ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሶስተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 4 ሺህ 47 ተማሪዎችን እንደሚያስመርቅ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አለምሸት ተሾመ በተለይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎችና ፕሮግራሞች በዶክትሬት ዲግሪ ከ20 በላይ፣ በድህረ ምረቃ ከ370 በላይ፣ በስፔሻሊቲ 18 እንዲሁም በመጀመሪያ ዲግሪ ከ3 ሺህ 500 በላይ እንደሚያስመርቅ ተገልጿል፡፡

በ1946 ዓ.ም የተመሰረተውና በግብርናው ዘርፍ ተማሪዎችን በማሰልጠን የመማር ማስተማሩን የጀመረው የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎችን ሳይጨምር እስካሁን ከ106 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በተለያዩ መስኮች አሰልጥኖ በማስመረቅ ለሃገር ያበረከተ አንጋፋ ተቋም ነው፡፡

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.