ህወሓት በአፋር በንፁሃን ላይ የከባድ መሳሪያ ጥቃትና ግድያ ፈጽሟል – የዓይን እማኞች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ህዝብን በጠላትነት የፈረጀው አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል ጭፍራ ንፁሃን ላይ የከባድ መሳሪያ ጥቃት መክፈቱን ከከተማዋ በስጋት የሸሹ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ቡድኑ ወደ ከተማዋ ሰርጎ ለመግባት መድፍና ሌሎች ከባድ መሳሪያዎችን መተኮሱን ይህም በንፁሃን ሃብትና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ነው የሚያስረዱት።
በሌላ በኩል ሰርገው የገቡ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች የአዕምሮ ህሙማንን ቀድመው መረሸናቸውን አብራርተዋል።
ትህነግ ምንም እንኳን በአፈቀላጤዎቹ ከህዝብ ጋር ጠብ እንደሌለው ደጋግሞ ቢገልፅም በሰራቸው አስነዋሪ የሽብር ስራዎች የህዝብ ጠላትነቱን ገልጿል ሲሉ የአይን እማኞች ገልጸዋል።
የአፋር አርብቶ አደሮችን ከብቶች መግደሉን እና እየነጠቀ አርዶ መብላቱንም አስረድተዋል።
ቡድኑ በወገን ጥምር ጦር እየደረሰበት ባለው ሽንፈት በመደናገጥ በንፁሃን ላይ የፈሪ በትሩን ማሳረፉ ብዙሃንን ለሞትና መፈናቀል ዳርጓልም ነው ያሉት።
ተፈናቃዮቹ የአሸባሪ ቡድኑ ግብአተ መሬት በአጭር ጊዜ እንዲፈፀም በግንባር እስከመሰለፍ የሚጠበቅብንን እናደርጋለን ብለዋል።
በአፈወርቅ እያዩ እና ፀጋዬ ወንደሰን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!



0
People reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share