ቴክ

“ሜታ” – አዲሱ የፌስ ቡክ ኩባንያ ሥያሜ

By Alemayehu Geremew

October 29, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፌስ ቡክ ኩባንያ ስያሜውን “ሜታ” በሚል መቀየሩን አስታወቀ፡፡

ፌስ ቡክ የኩባንያውን ስያሜ የቀየረው “ቨርችዋል ሪያሊቲ” የተባለውን አዲስ አገልግሎት እና ሌሎች ተጨማሪ ማሻሻያዎችን ለተጠቃሚዎቹ ማስተዋወቅ እና ብራንዱን ማደስ በመፈለጉ ነው ተብሏል፡፡

ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ኋትስ አፕ የተባሉት የኩባንያው የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ስያሜዎች ለውጥ እንደማይደረግባቸው የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡