Fana: At a Speed of Life!

ባለስልጣኑ ሲሰጣቸው የቆዩ ሰባት አገልግሎቶች በክልልና በከተማ አስተዳደሮች ሊሰጡ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም በፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን በኩል ሲሰጡ የነበሩ ሰባት አገልግሎቶች በክልልና በከተማ አስተዳደሮች እንደሚሰጡ ገለጸ።

ሚኒስቴሩ ከትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዘርፍ የክልል እና ከተማ አስተዳደር አመራሮች ጋር የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል።

በመድረኩ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ÷ በአዲሱ አደረጃጃት መሰረት ከዚህ ቀደም በፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን በኩል ሲሰጡ ከነበሩ አገልግሎቶች በፌደራል፣ በክልል እና በግሉ ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶች መለየታቸውን ገልጸዋል፡፡

ይህም አገልግሎቶቹን ለህዝብ ይበልጥ ተደራሽ እና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ለመስጠት ያስችላል ብለዋል።

በዚህ መሰረት ሰባት አገልግሎቶች በክልልና ከተማ አስተዳደሮች የሚሰጡ ሲሆን ይህንንም አስመልክቶ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ውይይት ከተደረገበት በኋላ በሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን ከትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.