Fana: At a Speed of Life!

የጉደር-ጌዶ 54 ኪሎሜትር የጥገና ግንባታ 92 በመቶ ተጠናቋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ-አምቦ-ባኮ-ነቀምት-አሶሳ የመንገድ አካል የሆነው የጉደር-ጌዶ 54 ኪሎሜትር ከባድ የጥገና ግንባታ ፕሮጀክት በማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
በአሁኑ ወቅትም ከመንገድ ፕሮጀክቱ 92 በመቶ የሚሆነው የከባድ ጥገና ስራው ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን÷ ቀሪ የፕሮጀክቱን ክፍል ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑንም ነው ባለስልጣኑ የገለጸው፡፡
መንገዱ በአገልግሎት መደራረብ የተጎዳ ሲሆን፥ ከሚያስገኘው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲሁም በየጊዜው እየጨመረ ከመጣው ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት አኳያ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ አድጎ ጥገናው እየካሄደ ነው ተብሏል፡፡
ለግንባታው 431 ሚሊየን 596 ሺህ 708 ስምንት ብር ከ75 ሣንቲም የተመደበ ሲሆን÷ ሙሉ በሙሉ በመንግሥት የሚሸፈን ይሆናልም ነው የተባለው፡፡
በፕሮጀክቱ ግንባታ ላይም አነስተኛ የአፈር ቁፋሮና ሙሌት፣ የሰብቤዝ እና የቤዝ ኮርስ ንጣፍ ስራ፣ ከፍተኛ የሆነ የአስፋልት ኦቨርሌይ ንጣፍ የውሃ ማስተላለፊያና የአቃፊ ግንብ ስራዎች በዋናነት ተሰርተዋል፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቱ ጉደር፣ ባቢች፣ ጎሮሶል እና ጌዶ ከተሞችን በቅርበት በማገናኘት የአካባቢውን ህብረተሰብ ደረጃውን የጠበቀ የመንገድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላል መባሉን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.