ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ ከባንክ የዘረፉ ሶስት ተጠርጣሪዎች ተያዙ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ )ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ከባንክ የዘረፉ ሦስት ተጠርጣሪዎች ወንጀሉን በፈፀሙ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እየተጣራ መሆኑንም ተገልጿል፡፡
የተደራጁ ዘራፊዎች ጥቅምት 17 ቀን ለ18 አጥቢያ 2014 ዓ.ም ሌሊት በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ከሚገኝ የሕብረት ባንክ ሲ ኤም ሲ ቅርጫፍ ውስጥ ነው ከአንድ የባንኩ የጥበቃ ሰራተኛ ጋር በመመሳጠር አንደኛውን ጥበቃ በመደብደብ ፣ በማፈን እና እጅና እግሩን በማሰር የዘረፋ ወንጀል ፈፅመው የተሰወሩት፡፡
ይሁን እንጂ አዲስ አበባ ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት አስፈላጊውን መረጃ በመለዋዋጥ ባደረገው ክትትል ወንጀሉ በተፈፀመ በሰአታት ጊዜ ውስጥ ሦስቱን ወንጀል ፈፀሚዎች ከዘረፉት 2 ሚሊየን 100 ሺህ 969 ብር ፣ 900 ዶላር ፣ 65 ድርሃም እንዲሁም 8 ሞባይሎች እና ግለሰቦቹ ለወንጀል ድርጊት ከተጠቀሙበት ኮሮላ መኪና ጋር በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡
የሕብረት ባንክ የሲ ኤም ሲ ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አቤኔዘር ጥሩነህ÷ ለአዲስ አበባ ፖሊስ አመራሮችና አባላት ምስጋና ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!