Fana: At a Speed of Life!

ባለስልጣኑ ለአፍሪካ ሃገራት ስልጠና መስጠት ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ባስገነባው የስልጠና ማዕከል የመሪነት ክህሎት የተሰኘ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

ከኬንያ የሚመጡ ሠልጣኞችንም በሚቀጥለው እሁድ ይቀበላል ነው የተባለው፡፡

ከጥቅምት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የመጀመሪያውን ስልጠና የሚወስዱት ከኬንያ ናሁሩ ከተማ በውሃና ፍሳሽ ላይ ከሚሠሩ ሦስት ድርጅቶች የተውጣጡ 11 የስራ ኃላፊዎች ናቸው፡፡

ከኬንያ የሚመጡት ሰልጣኞች ጥያቄ ካቀረቡት መካከል ሲሆኑ ስልጠናው በባለስልጣኑ ሰራተኞች የሚሰጥና ለስልጠናው የሚያስፈልገው የገንዘብ ድጋፍ በቪቴንስ ኢቪደስ ኢንተርናሽናል የሚሸፈን መሆኑን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.