ከውትድርና ሙያ ተሰናብቶ የነበረው ወታደር ዛሬ አሸባሪውን እያሳደደ ነው
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሚወደው የውትድርና ሙያ የተሰናበተው ወታደር ተመስገን ማሞ ዛሬ አሸባሪውን እያሳደደ ነው፡፡
ተመስገን ማሞ ይባላል፤ ነዋሪነቱ አዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ነው። ከዚህ በፊት በወታደርነት ሙያ አገሩን ለአምስት ዓመት ያህል አገልግሏል።
የአሁኑ አሸባሪ ቡድን በሰራበት ግፍ ያለምንም ማዕረግ ከሚወደው የወታደርነት ሙያ ሳይወድ በግድ እንዲሰናበት አድርጎታል።
አሁን ላይ በሹፍርና ሙያ ተሰማርቶ ቢገኝም እናት አገሩ ባደረገችለት ጥሪ ተመልሶ ወደ ሚወደው የውትድርና ሙያ በደስታ እንደተቀላቀለ ይናገራል።
ምልምል ወታደሩ፣ ለአምስት ዓመት ባገለገለበት ወቅት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በመወጣት ማዕረግ እንደነበረው ጠቅሶ፤ አሸባሪ ቡድኑ በዘረጋው የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ኢትዮጵያዊ ስሜት ባላቸው የወታደር አባላት ላይ በሚያደርሰው ግፍና ጫና የተነሳ ከሙያው እንዲገለል ተደርጓል።
በአሸባሪ ቡድን የሥልጣን ዘመን ወታደሮች ማዕረግ የሚያገኙት ባላቸው ብቃት ሳይሆን፥በብሔር ለሚመሳሰሏቸውና የእነሱን ዓላማ ለሚያስፈጽሙላቸው ብቻ ነበር።
ከሌላ ብሔር የሆነ ወታደር ሁልጊዜ በግምገማ እና አላስፈላጊ ስም በመለጠፍ ማዕረግ እንዳያገኙ ሲሰሩ እንደነበር አስታውሷል ሲል የዘገበው ኢፕድ ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!