Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያን ህዝበ ውሳኔ አስመልክቶ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያን ህዝበ ውሳኔ ውጤትን መሰረት አድርጎ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በነገው እለት ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አምስት ዞኖችና አንድ ወረዳ ራሳቸውን ችለው በክልልነት ለመደራጀት ሕዝበ ውሳኔ አካሂደዋል።
መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም በተካሄደው ድምፅ አሰጣጥ አምስቱ ዞኖች እና አንዱ ልዩ ወረዳ አንድ የጋራ ክልል መመሥረቱን ደግፈው 1 ሚሊየን 221 ሺህ 92 ድምፅ ሰጥተዋል።
በአንጻሩ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል አካል ሆነው መቀጠልን ደግፈው 24 ሺህ 24 ድምጽ መስጠታቸው ይታወቃል።
በውጤቱ መሠረትም የፌዴሬሽን ምክር ቤት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያን ህዝበ ውሳኔ ውጤትን መሰረት አድርጎ በነገው እለት ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የሕግ አማካሪ ዶክተር ዘለቀ ተመስገን በነገው ጉባኤ ከተያዙት አጀንዳዎች መካከል አንደኛው የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያን ህዝበ ውሳኔ ምርጫ ተከትሎ ውሳኔ መስጠት መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አምስት ዞኖችና አንድ ወረዳ እራሳቸውን ችለው በክልልነት ለመደራጀት በወሰኑት መሰረት ምክር ቤቱ የሚወስን ይሆናል ብለዋል።
ምክር ቤቱ 6ኛ የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የስራ ጊዜ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.