Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ተከለከለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19 ፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት መመለሱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አስታቋል፡፡
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰት ምክንያት የወጣውን መመሪያ ቁጥር 30/2013 መነሻ በማድረግ በከተማዋ የህዝብ እና ሌሎች ተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ በመወሰን በከፊል ማሻሻያ ተደርጎ ቆይቷል፡፡
በማሻሻያውም የማለዳውን የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ክልከላን በማንሳት ከሰዓት በኋላ ከ10 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2 ሠዓት ብቻ የእንቅስቃሴ ክልከላ በማድረግ ተግባራዊ ሲደረግ ነበር፡፡
በአሁኑ ሰዓት ከትምህርት ቤቶች መከፈት ጋር ተያይዞ በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት በከተማችን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ እየተስተዋለ በመሆኑ ÷ የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት መመለስ አስፈልጓል፡፡
በመሆኑም ከጥቅምት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በመመሪያው መሰረት ማንኛውም የጭነት፣ የማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎች ከማለዳ 12፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት እንዲሁም ከቀኑ 10 ሠዓት እስከ ምሽቱ 2 ሠዓት ሰዓት ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ እንዲሁም ጭነት መጫንና ማራገፍ እንደማይችሉ ቢሮው አስታውቋል፡፡
ስለዚህ የሚመለከታቸው አካላት በመመሪያው መሰረት ክልከላውን ተላልፈው በሚገኙ ግለሰቦች ላይ ቅጣት በመጣል ህጉን ተፈፃሚ እንዲያደርጉ ጥሪ መቅረቡን ከከተማ አስተዳደሩ የትራንስፖርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.