የትምህርት ቢሮው በተማሪዎች ላይ ምንም ዓይነት የምግብ መመረዝ እንዳልተገኘ ገለጸ
ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሀና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት 714 ተማሪዎች ላይ ምርመራ ተደርጎ ምንም አይነት የምግብ መመረዝ ችግር እንዳላጋጠመ ተገለጸ።
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ እንደገለጹት፥ በተካሄደው የህክምና በምርምራ ውጤቱ መሰረት ተማሪዎቹ የምግብ መመረዝም ሆነ ሌላ ምንም አይነት ሕመም እንዳልተገኘባቸው ተረጋግጧል።
በትምህርት ቤቱ ሰባት ተማሪዎች ላይ የማስመላስ ችግር ተስተውሎባቸዋል እንዲሁም ራሳቸውን ስተው ወደቁ የተባሉትንና ሌሎች ተማሪዎችን ጨምሮ ወደ ሕክምና ተቋም ተወሰደው ምርመራ የተደርጎላቸዋል።
ከተማሪዎቹ መካከል ሁለት ተማሪዎች አጥወለወለን ብለው የወደቁ ሲሆን ሌሎች ተማሪዎች ልጆቹን በማየታቸው የህመም ስሜት ተሰምቷቸዋል ተብሏል።
የትምህርት በሮ ኃላፊው አክለውም ÷የተማሪዎቻችንን ጤንነት ልክ እንደራሳችንና እንደቤተሰቦቻችን ያሳስበናል፤ ኃላፊነትም ይሰማናል” ነው ያሉት ፡፡
ከ 600 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች በምገባ ፕሮግራሙ ተጠቃሚ ስለሚሆኑ ጥንቃቄን ታሳቢ በማድረግ በጣም የተቀናጀ እና ጥራት ያለው ምግብ እየተዘጋጀ እንደሚቀርብም አስታውቀዋል።
የትምህርት ቤቱ የምገባ ኃላፊ አንቺነሽ ተስፋዬ እና የጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ሙሉጌታ ተስፋዬ መለጫውን በጋራ ስጥተዋል።
በሲሳይ ጌትነት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!