Fana: At a Speed of Life!

የደሴ ከተማ አሁንም ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ትገኛለች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደሴ ከተማ አሁንም ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እንደምትገኝ የደሴ ከተማ ሰላምና ደህንነት መምሪያ ገለፀ፡፡

ዛሬ ከቀትር በኋላ የከተማዋን ሰላም ለመረበሽ ኃሰተኛ ወሬን ሲያሰራጩ የነበሩ የሽብር ቡድኑ ተላላኪዎች ሀሳባቸው ሳይሳካላቸው ቀርቷል ፡፡

የደሴ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ሰይድ የሱፍ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ የወሎ ግንባር የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሀይል፣ ፋኖ እና ሚሊሻ የሽብር ቡድኑን እየደመሰሱት ይገኛሉ ፡፡

አሁን ከተማዋ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ነች ያሉት የደሴ ከተማ ሰላምና ደህንነትን መምሪያ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ሀሰን መሀመድ ህብረተሰብ ፀጉረ ልውጦችን በንቃት እንዲከታተል ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ከውልደቱ ጀምሮ ያለ በመሆኑ ህብረተሰቡ መደናገጥ የለበትም ቡድኑ አሁን በሞቱ ፋፃሜ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

በዘሩ ከፈለኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.