አሸባሪው ህወሓት መሣሪያዎቹን ሲጨርስ ምላሱን መተኮስ ጀምሯል- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ህብረተሰቡ የሐሰተኛ ወሬ ፈጣሪዎችንም ሆነ አስተላላፊዎችን ለሕግ እያቀረቡ ለማድረግ አካባቢውንና ቀዬውን አሁንም በንቃት መጠበቅ እንደሚኖርበት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አሳስቧል።
የመንግስት መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አሁን ባወጣው መግለጫ፥ “አሸባሪው ህወሓት መሣሪያዎቹን ሲጨርስ ምላሱን መተኮስ ጀምሯል ብሏል።
መግለጫው የሚከተለው ነው፡-
አሸባሪው ሕወሐት መሣሪያዎቹን ሲጨርስ ምላሱን መተኮስ ጀምሯል!
ሰሞኑን በደረሰበት ከባድ ምት ከተበታተነው ወራሪ ኃይል መካከል በጣት የሚቆጠረው በቦሩ ሜዳ አቅጣጫ በየወንዙ፣ በየጢሻውና በየሸለቆው ተደብቆ ከርሞ ነበር።
ለቀናት ከተደበቀ በኋላ ርሃብና ውኃ ጥም ሲከብደው የእሩምታ ተኩስ በመክፈት ከጉድጓድ እየወጣ የአካባቢውን ሕዝብ ለማደናገር ሞክሯል። አይጥ ከጉድጓዷ በራቀች ቁጥር እንደምትመታው፣ ይሄም የተቆረጠ አሸባሪ ወዲያው ተመትቷል።
የተቆረጠው ኃይል ወደ ሲኦል እየተሸኘ ባለበት፣ በውስጥ ያሠረጓቸው ኃይሎች ጁንታው ወሎ ዩኒቨርስቲ አካባቢን እንደተቆጣጠረ በማስመል የውሸት ፕሮፓጋንዳ እየነዙ ይገኛሉ።
ጀግናው መከላከያና መላው የጸጥታ ኃይላችን እነዚህን ባንዳዎች በመልቀም ርምጃ እየወሰደ ነው። ቦሩ ሜዳም ሆነ ከቦሩ ሜዳ ራቅ ያሉት አካባቢዎች በጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን እጅ ላይ ይገኛሉ።
ኅብረተሰቡ የሐሰተኛ ወሬ ፈጣሪዎችንም ሆነ አስተላላፊዎችን ለሕግ እያቀረበ አካባቢውንና ቀዬውን አሁንም በንቃት መጠበቅ ይኖርበታል።
የደሴ ከተማ ሕዝብ የሽብር ቡድኑን የሚያሸንፈው በጽናትና በትግል ብቻ ነው።
በወሬ የተገነባ ከተማ ስለሌለ፣ በወሬ የሚያዝ ከተማ አይኖርም! ሊኖርም አይችልም!
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!