Fana: At a Speed of Life!

ኤፍ ኤም ጣቢያዎች የውጭ አገር ፕሮግራሞችን ሊንክ አድርጎ ማሰራጨት ተከለከሉ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 19፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር ውስጥ የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች የውጭ አገር ፕሮግራሞችን ሊንክ አድርጎ ማስተላላፍ ከዛሬ ጀምሮ መከልከሉን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

በሀገር ውስጥ ፈቃድ ያልተሰጣቸው የውጭ ሀገር የሬዲዮ ጣቢያዎች ፈቃድ ባላቸው የአገር ውስጥ የኤፍ ኤም ማሰራጫ ጣቢያዎች አማካኝነት ፕሮግራሞቻቸውን ሲያስተላልፉ መቆየታቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሃመድ እድሪስ በሀገር ውስጥ የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች የውጭ ሀገር ፕሮግራሞችን ሊንክ አድርጎ ማስተላላፍ ከዛሬ ጀምሮ ተከልክሏል።

በውጭ ሀገራት የሚሰሩ የሬዲዮ ጣቢያዎች የሚተላለፉ ፕሮግራሞች የሀገር ውስጥ ህግና ስርዓትን ተከትለው አይካሄዱም፡፡

“በፕሮግራሞቹ የአንዳንድ ሀገራት አቋም መግለጫ ሲተለለፍ የሚታይበት እና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ግምት ውስጥ ያላስገባ ሲሆን ተስተውሏል” ብለዋል።

በተጨማሪም የሀገሪቷን ፖለቲካዊ ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያላስገቡ ፕሮግራሞችም ሲተላላፉ እንደነበርም አስታውሰዋል።

እነዚህ አካላት በሀገር ውስጥ ፈቃድ ያላገኙ በመሆናቸው የሚተላለፉ መርሃ ግብሮችን በመከታተል ግብረ መልስና የማስተካከያ ሃሳብ ለመስጠት የሚቻልበት ሁኔታ አለመኖሩንም ገልጸዋል፡፡

በሀገር ውስጥ የሚያስተላልፉ የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎችም ፕሮግራሞቹ ላይ የሚያደርጉት ቁጥጥር አነስተኛ መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የተጠቀሱትን ሃሳቦች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ባለስልጣኑ ከዛሬ ጀምሮ ከውጭ ሚዲያዎች ወደ ሀገር ውስጥ የኤፍ ኤም ጣቢያዎች ሊንክ አድርጎ ማስተላለፍን ከልክሏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.