Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያን ህዝበ ውሳኔ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የስራ ጊዜ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን ዛሬ ያካሂዳል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ በሚካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልልና ህዝበ ውሳኔ ውጤትን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በቅርቡ የተካሄደውን የህዝብ ውሳኔ ውጤት ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በደብዳቤ ማሳወቁን ምክር ቤቱ ይፋ አድርጓል፡፡
ከምክር ቤቱ ውሳኔ በኋላ የደቡብ ክልል ምክር ቤት በሚያቀርበው ስብሰባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል 11ኛ ክልል መሆኑን እውቅና ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ:- ኢዜአ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.