Fana: At a Speed of Life!

በጦርነቱ የታጣውን ምርት ለማካካስ የቀውስ ወቅት ዕቅድ ይተገበራል – ግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ፣ በአማራና በአፋር ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት የታጣውን ምርት ለማካካስና እንስሳትን ለመተካት የቀውስ ወቅት ዕቅድ እንደሚተገበር የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር መለሰ መኮንን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት÷ በአሸባሪው ህወሓት በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት በግብርናው ሥራ ላይ በተከሰተው መስተጓጎል የምርት እጥረት እንዳይከሰት ግብርና ሚኒስቴር ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

ከሠብል ልማቱ ባሻገር በጦርነቱ ምክንያት አርሶ አደሩ ያጣውን ምርት እና እንስሳትን ለማካካስና ለመተካት የቀውስ ወቅት ዕቅድ ይተገበራል ተብሏል፡፡

በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች ÷ አካባቢያቸው ነጻ እስካልሆነ ድረስ ተመልሰው የእርሻ ሥራን ለማከናወን ስለማይችሉ እንደ ክልልም እንደ ሀገርም ሁኔታውን ያገናዘበ ዕቅድ እየተዘጋጀ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ከእቅዱ በመነሳትም ትግበራ የጀመሩ ክልሎች መኖራቸውን ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል፡፡

በትግበራው በድንገተኛ አደጋ ተፈናቅለው ከሥራ እንቅስቃሴ ውጪ የሆኑትን የመታደግ ሥራዎች እንደሚተገበሩ፣ በሚለቀቁ አካባቢዎች አርሶ አደሮችን ወደ እርሻ ሥራቸው ለመመለስ ዕቅድ መያዙንም ነው የተገለጸው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.