Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነት መጠበቅ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው-የሃይማኖት አባቶች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነት መጠበቅ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን የሃይማኖት አባቶች ገለፁ።
በኢትዮጵያ በኃይማኖት ተቋማት መካከል ያለው መቀራረብ ለብሔራዊ መግባባት ፋይዳው የጎላ መሆኑንም አንስተዋል።
ኢዜአ ያነጋገራቸው የሃይማኖት አባቶች እንዳሉት፥ኀብረተሰቡ ተቀራርቦና አንድነቱን አጠናክሮ ለሀገር ግንባታ በጋራ ሊሰራ ይገባል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሃይማኖት አባት መልአከፀሀይ በቀለ ተሰማ፥ የሃይማኖት ተቋማት የአገርን ሰላም ለመጠበቅና ልማት ለማረጋገጥ በጋራ እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የሃይማኖት ተቋማት በአገር ጉዳይ ላይ ተቀራርበው መስራታቸው ለብሔራዊ መግባባት ፋይዳው የጎላ መሆኑንም ነው ያነሱት።
መንግስት ሰላምንና መቻቻልን የሚያጎለብቱ የውይይት መድረኮችን በማመቻቸት በዜጎች መካከል ያለው መቀራረብ ይበልጥ እንዲጠናከር መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።
ሰላም የሚጀመረው ከራስ መሆኑን በመጥቀስ፤ ሀገር ሰላምን ማስጠበቅ የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን ተናግረዋል።
ሁሉም ዜጋ ለሀገር አንድነት መጠበቅ የበኩሉን ሚና እንዲወጣም ነው መልአከፀሀይ በቀለ ተሰማ ጥሪ ያቀረቡት፡፡
“ሀገር የምታድገው እርስ በርስ ስንደጋገፍ ነው” ያሉት ደግሞ የእስልምና ሃይማኖት አስተማሪ የሆኑት ሼህ ሰይድ አብዶ ናቸው።
የኢትዮጵያን ልማት ለማረጋገጥ ህዝብና መንግስት ተቀራርበው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ጠቅሰው ፥የተሳሳቱ አመለካከቶችን በማረም አገርን በትብብር ማልማት እንደሚገባ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን መካነእየሱስ የሃይማኖት አባት ቄስ ከበደ አበባው በበኩላቸው ፥ ህብረተሰቡ አንድነቱንና ህብረቱን ጠብቆ እንዲሄድ የሃይማኖት መሪዎች ሚና ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት በሃይማኖት ተቋማት መካከል ያለው መቀራረብና ትብብር በህብረተሰቡ መካከል መግባባት ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል።
በስነ-ምግባር የታነጸ መልካም ትውልድ ለመፍጠር ሁሉም የበኩሉን ሚና እንዲወጣም የሃይማኖት አባቶቹ ጥሪ አቅርበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
13
Engagements
Boost Post
12
1 Comment
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.