ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 225 ተማሪዎች በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ በ7ኛ ዙር መርሃ-ግብሩ አስመርቋል ።
ተመራቂዎቹ በመደበኛ፣ በርቀትና ተከታታይ መረሃ ግብር የሰለጠኑ ሲሆን ከመካከላቸውም 485 ሴቶች መሆናቸው የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።
ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር ዶክተር መኩሪያ ኃይሌ፣የዩኒቨርሲቲው ቦርድና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!