የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱርዶ ከኢትዮጵያ ሴት ስራ ፈጣሪዎች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱርዶ ከኢትዮጵያዊያን ሴት ስራ ፈጣሪዎች ጋር ተወያዩ።
ካለፈው አርብ ጀምሮ ለስራ ጉብኝት በአዲስ አበባ የሚገኙት ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ቱርዶ በዛሬው እለት ነው ከኢትዮጵያዊያን ሴት ስራ ፈጣሪዎች ጋር የተወያዩት።
በውይይታቸውም ሴት ስራ ፈጣሪዎች በስራ ሂደታቸው በሚያጋጥሟቸው ችግሮች እና በቴክኖሎጂ በመታገዝ የሴት ስራ ፈጣሪዎችን ተግባር መደገፍ በሚያስፈልጉባቸው ሁኔታዎች ላይ ተወያይተዋል።
ኢትዮጵያ ከዜጎቿ ውስጥ 70 በመቶ ወጣት እንደመሆኑ መጠን ስራ ፈጣሪዎችን መደገፍና ማብዛት በርካታ ወጣቶች የስራ እድል እንዲያገኙ የራሱን አስተዋፅኦ እንደሚያደርግም በውይይታቸው ላይ ተነስቷል።
የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ትሩዶ ባለፈው አርብ ነበር ይፋዊ የስራ ጉበኝት ለማድረግ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት።
ትናንትናም ከፕሬዚዳንት ሳህለወረቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽ እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸው ይታወሳል።
በመታገስ አየልኝ