Fana: At a Speed of Life!

የፀጥታ ሀይሉ በሚፈጽመው የተቀናጀ ማጥቃት አሸባሪው ቡድን ላይ ድል እየተቀዳጀ ነው -የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  የጸጥታ ሀይሉ በሚፈጸመው የተቀናጀ ማጥቃት የአሸባሪውን ህወሃት ቡድን እየደመሰሰና ድል እየተቀዳጀ መሆኑን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ተሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የአገልግሎቱ ሀላፊ ሚኒስትር ዶክተር ለገሠ ቱሉ እንደገለጹት፥ የፀጥታ ሀይሉ በሚፈጸመው የተቀናጀ ማጥቃት ድል እየተቀዳጀ ነው።

ቡድኑ ባለፋት ጥቂት ቀናት ያለውን ሀይል አሰባስቦ በወረባቦ፤በተሁለደሬ እና በጭፍራ ጥቃት መክፈቱን አስታውሰዋል።

የፀጥታ ሀይሎች በወሰዱት የአጸፋ እርምጃ “የአሸባሪው ህወሃት አባላት ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል” ብለዋል።

አየር ሀይሉ እየወሰደ ባለው እርምጃም በተሳካ መልኩ የአሸባሪው ህወሃት መጠቀሚያዎችን ማውደም መቻሉንም አብራርተዋል።

አሁንም ቡድኑ እኩይ ድርጊቱን የቀጠለ መሆኑን አመልክተው፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ከምን ጊዜውም በላይ በአንድነት መነሳት እንዳለበት አብራርተዋል።

“በሁሉም የአገሪቷ አካባቢ መዝመት የሚችል ሁሉ ራሱን ዝግጁ ማድረግ አለበት” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ህዝቡ እንደሰራዊት በሁሉም መስክ ለአገሩ አስተዋጽኦ ለማድረግ ራሱን ማዘጋጀት እንዳለበት ተናግረዋል።

ከዚህም  ባለፈ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የአገሪቷ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዲቀላጠፍ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚጠበቅም መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.