Fana: At a Speed of Life!

ዋናው የእድገት መንገድ እያንዳንዱን እድልና አቅም በአግባቡ መጠቀም መቻል ነው- ኢ/ር ታከለ ኡማ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ ዋናው የእድገት መንገዳችን እያንዳንዱን እድልና አቅም በተገቢው መንገድ መጠቀም መቻል ነው ሲሉ የማእድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለጹ።
ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጣቸው ላይ፥ ችላ የምንለውና የምናባክነው ሀገራዊ ሀብት አይኖርም ብለዋል፡፡
በዛሬው እለት ከውሀና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋና ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሸብር ባልቻ ጋር በመሆን አርሲ ኢተያ አካባቢ የሚገኘውን ቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተናልም ነው ያሉት።
ፕሮጀክቱ በሚኖረው ሁለት ምእራፍ ግንባታ 150 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት ይችላል።
ይህ ለሀገራችን የኤሌክትሪክ ሀይል ተጨማሪ አቅም የሚሰጥ ሲሆን በቀጣይ ጊዜያም በተለያዩ ቦታዎች እንዲህ ያሉ የጂኦተርማል ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ለመጀመር ጥናት እየተካሄደ እና በሂደት ላይ የሚገኝ ሲሆን እንደ አሉቶ ላንጋኖ፣ኮርቤቲና ተንዳሆ ላሉ የጂኦተርማል ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችም በፍጥነት እንዲጠናቀቁና የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት እንዲሰጡ ጠንካራ ድጋፍ የምናደርግ ይሆናል ብለዋል፡፡
ኢትዩጵያ ከጂኦተርማል 10ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት የጂኦሎጂካል ሰርቬይ ኢንስቲትዩት ባደረገው ቅድመ ጥናት አረጋግጧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግ
+3
0
People reached
40
Engagements
Boost Post
38
2 Comments
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.