ለሀገር ህልውና መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን – የማዕከላዊ ጎንደር የመንግስት ሰራተኞች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር የማዳን ጊዜው አሁን በመሆኑ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን ተሰልፈው የህልውና ዘመቻውን በመቀላቀል መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የመንግስት ሰራተኞች አስታወቁ፡፡
የዞኑ የመንግስት ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ሰላምና ለህልውና ዘመቻው መሳካት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በሚያደርጉበት ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ሰራተኞቹ እንደተናገሩት፤ ሀገር አፍራሹ የህወሃት የሽብር ቡድን በወሎ ግንባር የከፈተው ጦርነት በተባባረ የህዝብ ልጆች መስዋዕትነት በግብአተ መሬቱ ይጠናቀቃል፡፡
በውይይቱ ተሳታፊ የሆኑ ሰራተኞች በሰጡት አስተያየት ፥ የህልውና ዘመቻውን በመደገፍ ከአሁን ቀደም የወር ደመወዛቸውን መለገሳቸውን አስታውሰዋል።
ሀገር ከሌለ የመንግስት ስራም ሆነ ሰራተኛ ሊኖር እንደማይችል ጠቅሰው ፥ወደ ግንባር ዘምተው ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመሰለፍ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
”የሽብር ቡድኑ በአፋርና አማራ ክልል በመውረር ዜጎችን ለሞት፣ ለስደትና ለስቃይ መዳረጉ በእጅግ የሚያም ነው” ብለዋል።
የሽብር ቡድኑን ሀገር የማፍረስ ተልዕኮ ለመቀልበስ በአንድነትና በህብረት የምንነሳበት ጊዜ አሁን በመሆኑ ግንባር ድረስ ለመዝመት ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በታሪኳ ከህወሃት የበለጠ ፋሺስታዊ የሽብር ቡድን ገጥሟት እንደማያውቅም ገልጸዋል፡፡
የወሎ ህዝብ የሽብር ቡድኑን በመፋለም እያደረገ ያለውን የጀግንነት ተጋድሎ ያወደሱት አሰተያየት ሰጪዎች፤ የህልውና ዘመቻውን በፍጥነት ለመቀላቀል ዝግጁ መሆናቸውን ነው ያስታወቁት፡፡
የብልጽግና ፓርቲ የዞኑ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፈንታሁን ስጦታው በበኩላቸው፤ የማዕከላዊ ጎንደር የህወሃት የሽብር ቡድን የከፈተበትን ወረራ መክቶ በመቀልበስ ግንባር ቀደም ተሳትፎ ካደረጉ ዞኖች አንዱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የመንግስት ሰራተኛው የህልውና ዘመቻው እንዲሳካ የወር ደመወዙን ከመለገስ ጀምሮ ለሰራዊቱ ስንቅ በማዘጋጀትና ግንባር ድረስ በመላክ ያደረገው የደጀንነት ተሳትፎ እጅግ የሚያኮራና የሚያበረታታ ነው ብለዋል፡፡
የሽብር ቡድኑን ወረራና ዝርፊያ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በማስቆም ከአማራ ክልል ሙሉ በሙሉ ጠራርጎ ለማስወጣት ለሚደረገው ህዝባዊ ዘመቻ የመንግስት ሰራተኛው የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በውይይት መድረኩ በዞኑ በ21 የሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችና የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የአስተዳድሩ አመራሮች ተሳታፊ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግ

0
People reached
0
Engagements
–
Distribution Score
Boost Post
Like
Comment
Share