ኢትዮጵያን ከጠላቶቿ ለመታደግ ስልጠና ላይ ያሉትን ጀግኖች ለማጀገን ስልጠና ማዕከል ድረስ የሄዱት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ኢትዮጵያን ከገጠማት ችግር ለመታደግና ጠላቶቿን ለመመከት ከሙያቸው ባሻገር ወደ ግንባርም እንዘምታለን ብለዋል፡፡
በየትኛውም አጋጣሚ ከፊት የሚሰለፉት የኪነጥበብ ባለሙያዎች÷ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተነሳውን አሸባሪ ህወሓት ከሙያቸው ባሻገር ግንባር ድረስ ሄዶ ለመፋለም የቀደማቸው እንዳልነበረ ትውልድ የሚመሰክረው ታሪክ አኑረዋል።
ባለሙያዎቹ ለሀገራዊ ጉዳዮችም ፈጣን ምላሽ በመስጠት ብዙ ሰርተዋል፤ እየሰሩም ይገኛሉ።
በአሁኑ ወቅትም መንግስት እያከናወነ የሚገኘውን የህልውና ዘመቻ ለመደገፍና የአገር መከላከያ ሰራዊቱን አለንላችሁ፤ ከጎናችሁ ነን ለማለት ተሰብስበው በልምምድ ረጅም ጊዜን አሳልፈዋል።
በቅርቡ በወታደራዊ ማሰልጠኛ የሚገኙ ምልምል ወታደሮችን ለማነቃቃት ሲጓዙ ማንም ወደየት እንደሚሄዱ የሚያውቅ አልነበረም።
እንዲህ ያለው የጥበብ ስራ በኢትዮጵያ የጦርነት ታሪክ ውስጥ ጉልህ ድርሻ እንዳለው የሚታወቅ ነው።
በታሪኳ ሽንፈትን የማትቀበለው የአፍሪካ ተምሳሌት የሆነችው ኢትዮጵያ በየዘመኑ የሚፈጠሩ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በፍቅር እየተቀባበሉ ዛሬም ድሉን ለማፍጠን ከጎኑ ተሰልፈዋል፡፡
ስለሀገር መች ይተርፋል፤ ማንስ አስችሎት ይቀመጣል?
የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ኢትዮጵያን ከገጠማት ችግር ለመታደግና ጠላቶቿን ለመመከት ከሙያቸው ባሻገር በድጋሜ ግንባር ድረስ በመሄድ ታሪክ የሚሰሩ መሆናቸውንም ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ አረጋግጠዋል፡፡
በሙዚቃዎቻቸው ውስጥ ኢትዮጵያን ሳያነሱ ቢያልፉ እርግማን እስኪመስላቸው ድረስ የሀገራቸውን ፍቅርና ክብር ይገልጻሉ።
”ኢትዮጵያ” በሚለው ሥራዎቻቸው ውስጥ የአፍሪካ መዲናና የጥንት አባቶችን ታሪክ እያወሱ፤ ለጠላቶቿ የማትበገር ሀገር መሆኗን በትውልዱ ልብ ውስጥ እንዲቀር ያደረጉ ባለታሪክ ናቸው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!