አሸባሪው ህወሃት ሰሜን እዝ ላይ የፈፀመው ጥቃት ጥቅምት 24 ታስቦ ይውላል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው የህወሃት ቡድን ሰሜን እዝ ላይ የተፈፀመው የክህደት ተግባር እና ጥቃት ጥቅምት 24 ታስቦ እንደሚውል ተገለፀ።
የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፥ ዕለቱ “አልረሳውም፥ እኔም የኢትዮጵያ ሰራዊት ነኝ”በሚል መሪ ቃል ታስቦ እንደሚውል ተናግረዋል።
ዕለቱ የመከላከያ ሰራዊቱ እየከፈለ ያለውን መስዋዕትነት ለማሰብ፣ ሁሉም ህዝብ የሀገሩ ጠባቂ እና ሰራዊት መሆኑን እንዲሁም ከመከላከያ ጎን መሆኑን የሚያሳይበት ይሆናል ነው ያሉት፡፡
ጥቅምት 24 በሚኖረው ስነ ስርዓት ላይ መስዋዕት የሆኑ የሰራዊት አባላትን እና የቡድኑን ክህደት ለማስታወስ በዕለቱ ጠዋት 3 ሰዓት ጀምሮ ሁሉም ህዝብ ለ45 ሰኮንዶች እጃቸውን ደረታቸው ላይ በማድረግ ይቆያሉ፡፡
በተጨማሪም የሻማ ማብራት እና ደሙን እየገበረ ላለው ሰራዊት የደም ልገሳ መረሃ ግብር እንደሚከናወን ነው ሚኒስትር ዴኤታው የገለጹት፡፡
በበርናባስ ተስፋዬ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!