Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሀገራት አቅም ግንባታ ላይ እየተሰራ ነው- የአፍሪካ ህብረት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮና ቫይረስን ለመግታት የሀገራት የመከላከል አቅም ግንባታ ላይ እየተሰራ መሆኑን የአፍሪካ ሀብረት አስታወቀ።

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው 33ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የህብረቱ የማህበራዊ ጉዳይ ኮሚሽን በወቅታዊ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የአፍሪካ ህብረት የማህበራዊ ጉዳይ ኮሚሽነር አሚራ ኤልፋዲል መሃመድ፥ የኮሮና ቫይረስ እስካሁን በአፍሪካ ምድር አንዳልተከሰተ አስታውቀዋል።

15 የአፍሪካ ሀገራት ለኮሮና ቫይረስ ከፍተኛ ተጋላጭ ነው ተብለው እንደተለዩ እና ቫይረሱ ከመከሰቱ በፊት ለመከላከል የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ አንደሆነም ተገልጿል።

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል አምስት ቀጠናዊ የትብብር ማእከላት በኢትዮጵያ፣ በግብፅ፣ በጋቦን፣ በጊኒ እና ዛምቢያ ተከፍተው እየተሰሩ መሆኑንም ነው የተነገረው።

ከዚህ በተጨማሪም የአፍሪካ ህብረት ደካማ የጤና ስርዓት ላላቸው ሀገራት የአቅም ግንባታ ስራ እየሰራ መሆኑም በመግለጫው ተነስቷል።

ኮሮና ቫይረስን እንዴት መከላከል ይቻላል የሚለው ላይም የህብረቱ የማህበራዊ ጉዳይ ኮሚሽን ስልጠና እየሰጠ መሆኑም ነው የተገለፀው።

በምስክር ስናፍቅ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.