የአፍሪካ ህብረት መሪዎች በሊቢያ የሰላም ጉዳይ ላይ ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ከ33ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን በሊቢያ የሰላም ጉዳይ ላይ መክረዋል።
መሪዎች በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ባካሄዱት ስብሰባ የሊቢያ ግጭትን መፍታት ላይ ትኩረት ሠጥተው ውይይት ማድረጋቸው ነው የተጠቀሰው።
በውይይት መድረኩ ላይም በሊቢያ የአፍሪካ ሀገራት ሰላም አስከባሪ ሀይልን እንዴት አቋቁሞ ይላክ የሚለው ተነስቷል ነው የተባለው።
የሊቢያ የሰላም ጉባዔን የመሩት የኮንጎው ፕሬዝዳንት ዴኒስ ሳሱ ኑጉሶ፥ የሊቢያ ጉዳይ ሁሉንም ሊያሳስብ የሚገባው ጉዳይ መሆኑን አንስተው።
በውይይት መድረኩ ላይ የአፍሪካ ሀገራት ሰላም አስከባሪ ሀይል ጉዳት ተነስቷል፤ በዚህ ላይ የአፍሪካ ህብረት ፀጥታ ምክር ቤት አባላት ውሳኔ እየተጠበቀ ነው ብለዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም በሊቢያ ያለውን ግጭት ለማስቆም የአፍሪካ ህብረት የላቀ ሚና እንዲጫወት ጥሪ ማቅረቡም ነው የተገለፀው።
ምንጭ፡- አልጀዚራ