Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል 131 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይሰበሰባል ተብሎ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮው የምርት ዘመን በአማራ ክልል 131 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ቃልኪዳን ሺፈራሁ በዘንድሮው የምርት ዘመን 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን ጠቅሰው ÷ ከዚህ ውስጥ 131 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

ሆኖም ተዘርተው በአሸባሪው ሕወሓት ጉዳት እየደረሰባቸው ያሉ ምርቶች መኖራቸውን ገልጸዋል።

የጉዳቱን መጠንና የሚኖረውን ተፅእኖ በሚመለከት በተወሰነ መልኩ ጥናት መደረጉን ምክትል ቢሮ ሃላፊው ገልጸው ÷ በዝርዝር ለማረጋገጥ ግን ተጨማሪ ጥናት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

በፍጥነት ወራሪው ሃይል ከተወገደ በኋላ የተበላሹ የመስኖ ተቋማት ካሉ የማስተካከል ፤ በተለይ እንደ ግብርና ቢሮ “ትኩረት መደረግ ያለበት ነገር ምንድን ነው?” የሚለውን የመለየት ሥራ እየተሰራ እንደሆነ የገለጹት ምክትል ቢሮ ሃላፊው እያንዳንዱን አካባቢ በመስኖ ልማት ለመሸፈን ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

በክረምቱ በአሸባሪው ሕወሓት የጠፋውን ምርት የማካካስ ስራ በቀጣይ ይሰራል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.