የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከዋግኸምራ ዞን ተፈናቅለው በእብናት ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ16 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ማህበሩ ከዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ጋር በመተባበር ነው ድጋፉን ያደረገው፡፡
ድጋፉ ለ3 ሺህ አባዎራዎች የተደረገ ሲሆን÷ ለእያንዳንዱ አባዎራ የስንዴ ዱቄት፣የምግብ ዘይት፣ ብስኩቶች፣ ምንጣፍ ፣ ብርድልብስ፣ የመመገቢያና የማብሰያ ዕቃዎች፣ ጀሪካን፣ ሳሙና እና የሴቶች የንጽህና መጠበቂያን ያካተተ ድጋፍ መደረጉን ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!