የመተከል ዞን የሚሊሻ አባላት ከመከላከያ ሰራዊት ጎን እንደሚሰለፉ አረጋገጡ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የመተከል ዞን የሚሊሻ አባላት ከጀግናው የሃገር መከላከያ ሰራዊት ጎን እንደሚሰለፉ አረጋገጡ ።
አባላቱ በግልገል በለስ ከተማ ከመተከል ኮማንድ ፖስት የተቀናጀ ግብረ ሃይል ተወካይ አስተባባሪ ኮሎኔል በስፋት ፈንቴ ፣ ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጋሹ ዱጋዝ ፣ ከከፍተኛ የመከላከያ አመራሮች እና የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።
ከሚሊሻ አባላቱ መካከል ጋሊድ ድሌት እና ብርሌ አድማሱ እንደተናገሩት ÷ ከጀግናው መከላከያ ሰራዊት ጎን በመሰለፍ የትኛውንም አይነት መስዋዕትነት በመክፈል አሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።
ኮሎኔል በስፋት ፈንቴ ÷ የአሸባሪው ቡድን ቅጥረኛ ሃይሎችን ለመደምሰስ ከፀጥታ ሃይሎች ጎን በመሆን ያሳያችሁት ቆራጥነት ለመድገም ከሰራዊታችን ጎን ለመሰለፍ መወሰናችሁ ያኮራል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!