Fana: At a Speed of Life!

ጠላትን በርትታችሁ ታገሉ – በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የደቡብ ካሊፎርንያ ሀገረ ስብከት

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “በስደት መኖር ስለማይቻል እንዲሁም ሀገር ለቅቆ የትም ስለማይደረስ ጠላትን በርትታችሁ ልትታገሉ ይገባል” ሲሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ካሊፎርንያ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መምህር ሀብተማሪያም እማኛው ተናገሩ፡፡

የደቡብ ካሊፎርንያ ሀገረ ስብከት በወቅታዊ ሀገራዊ ችግር ለተፈናቀሉ ወገኖችም ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብ ድጋፍ ማድረጓ ነው የተመለከተው።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ካሊፎርንያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ በርናባስ ÷ “እናንተ በግፈኞች የተሰደዳችሁ ወገኖች፣ ወገኖቻችሁ ደጀን ስለሆኑላችሁ ደስታ ሊሰማችሁ ይገባል” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ስለሚደግፏችሁ ጥንካሬ ሊሰማችሁ ይገባል ብለዋል።

የሰሜን ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሠላምይሁን ሙላት በበኩላቸው ÷ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ካሊፎርንያ ሀገረ ስብከት ላደረገው ድጋፍም አመስግነዋል። በክተት አዋጁ መሠረት ተፈናቃይ ወጣቶችና ለትግል ብቁ የኾኑትን ጀግኖች በማደራጀት ወደትግሉ የሚገቡበት አሠራር እየተሠራ ነው ብለዋል።

ተፈናቃዮችም በበኩላቸው÷ ለትግል ዝግጁ መሆናቸውንና ዘመቻውን በመቀላቀል ለስደት የዳረጋቸውን ጠላት ለመደምሰስ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡

በዞኑ አሸባሪው ቡድን ባደረገው ወረራ ከ135 ሺህ በላይ ወገኖችተፈናቅለው እንደሚገኙም ከአሚኮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.