Fana: At a Speed of Life!

አመራሩና ህዝቡ የተግባር አንድነት ፈጥሮ ሀገርን መታደግ ይኖርበታል ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በዛሬው እለት ውይይት አካሂደዋል፡፡
አሸባሪው ህወሓት እና ተላላኪዎቹ ኢትዮጵያን እኔ ካልመራኋት ትፍረስ፤ ትበታተን የሚል አላማን አንግበው እየሰሩ መሆናቸውን ሁሉም በሚገባ ሊገንዘብ እና ሊያውቅ ይገባል ሲሉ ከንቲባዋ ገልጸዋል፡፡
“ይህን የተደቀነብንን ሀገር የማፍረስ አደጋ ለመቀልበስ ሁሉም አመራር ተቀናጅቶ ፣ ተናቦ እና የተግባር አንድነት ፈጥሮ ሀገርን ከብተና ውአገር አልባ ከማድረግ ክፉ ምኞት መታደግ እንዳለበትም” ነው የተናገሩት፡፡
የከተማ አስተዳደሩ እና መላው ነዋሪዎች እንደከዚህ ቀደሙ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን እና ሌሎች የጸጥታ አካላትን በሞራል እና በሎጅስቲክ በመደገፍ ደጀንነቱን ማሳየት ይኖርበታልም ብለዋል፡፡
ወጣቶችም እንደከዚህ ቀደሙ የመከላከያ ሰራዊቱን በመቀላቀል ከፍተኛ መስዋዕትነት የተከፈለበትን ሀገራዊ ለውጥ በፅንፈኛ ቡድኖች እንዳይቀለበስ መታገል እንዳለባቸው ከንቲባዋ ጥሪ ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያ ያኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ህዝብን ባሳተፈ መልኩ የአሸባሪውን ተላላኪዎች በተደራጀ መንገድ በማጋለጥና አሳልፎ በመስጠት የአካባቢዉን ሰላም ከማስጠበቅ ጎን ለጎንም÷ በጦርነቱ የተፈናቀሉ ዜጎችን የመደገፍ እና እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገዝንበዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.