የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት የሚያስገነባው የአይነስውራን ት/ቤት ተጎበኘ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ፅህፈት ቤታቸው እያስገነባ ያለውን የአይነስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ጎብኝተዋል፡፡
ጽህፈት ቤቱ በ400 ሚሊየን ብር የሚያስገነባው ትምህርት ቤት 320 አይነስውራንን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን÷ ለአይነስውራኑ በሚሆን መልኩ እየተገነባ ነው ተብሏል፡፡
የአዳሪ ትምህርት ቤቱ ግንባታ በ2012 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን፥ በቀጣዮቹ ሰባት ወራት ግንባታው ይጠናቀቃል ነው የተባለው።
በአዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ የሚገነባውን ትምህርት ቤቱ በ3 ነጥብ 3 ሄክታር ላይ ያረፈ መሆኑም ተገልጿል።
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የግንባታው ሂደት በተባለለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ አስቻይ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ከባለሙያዎች ጋር መክረዋል።
አዳሪ ትምህርት ቤቱ በውስጡ የአስተዳደር ህንፃ፣ የአስተማሪዎች መኖሪያ፣ የተማሪዎች መኖሪያ፣ የእንግዳ ማረፊያ፣ ቤተ መፅሐፍት፣ የመመገቢያ አዳራሽ እና የኮምፒውተር ላቦራቶሪ የተሟላለት ነው፡፡
በፍሬህይወት ሰፊው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!