Fana: At a Speed of Life!

የአዊ ብሔረሰብ ነዋሪዎች ወደ ግንባር ለመዝመት መዘጋጀታቸውን አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ነዋሪዎች ለክተት ጥሪው ፈጣን ምላሽ በመስጠት ወደ ግንባር ለመዝመት መዘጋጀታቸውን የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ እንግዳ ዳኛው አስታወቁ፡፡

የብሔረሰብ አስተዳደሩ ነዋሪዎች ÷ ሽብርተኛው የትህነግ ወራሪ ቡድን አማራን ለማጥፋት አሰፍስፎ የተነሳ መሆኑን በመረዳት በግንባር ለመፋለም መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡

የሽብርተኛውን ትህነግ ተላላኪዎች ለመመከት በግንባር የማይሳተፈው ኅብረተሰብም አካባቢውን በንቃት እየጠበቀ መሆኑን አቶ እንግዳ ገልጸዋል፡፡

በየደረጃው ያሉ የሥራ ኃላፊዎችም ሕዝብን በማደራጀት አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ ታሪካዊ ኃላፊነት እየተወጡ መሆኑን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.