ኢትዮጵያን ሊያጠፋ የመጣን ጠላት የማይፋለም ኢትዮጵያዊ ሊኖር አይገባም – ኢሕአፓ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያንን ሊያጠፋ የመጣን ጠላት የማይፋለምና ኢትዮጵያን ለማዳን በሚካሄደው የህልውና ዘመቻ የማይሳተፍ ኢትዮጵያዊ ሊኖር አይገባም ሲል ኢሕአፓ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) መንግስት ከሰሞኑ ያቀረበው የክተት ጥሪ እንደሚደግፍ በመግልጽ ህዝቡ ራሱን አደራጅቶ የአሸባሪውን ቡድን አገር የማፍረስ ትግል እንዲቀለብስም ጥሪ አቅርቧል።
ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት እንዳሉት፥ የአሸባሪው ሕወሃት ገና ከጥንስሱ ዓላማው ኢትዮጵያን ማፍረስና ታላቋን አገረ-ትግራይ መመስረት ነው።
በደርግ ዘመን የኢትዮጵያ አንድነት አቀንቃኝ ሃይሉ መግባባት ባለመቻሉ ለአሸባሪው ሕወሃት ወደ ስልጣን መምጣት መልካም እድል እንደፈጠረለት አስታውሰው፤ ኢትዮጵያን ዘርፎ አገራዊ ህልውናዋን የማፍረስ ህልሙን ለማሳካት ሲጥር እንደኖረ አስረድተዋል።
በዚህም ኢትዮጵያውያንን በዘር በመከፋፈል ዘረኝነት ስር እንዲሰድ ማድረጉን ጠቁመው፤ አንጡራ ሀብቷን ዘርፎ ማሸሹን ብሎም “ለዛሬ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የዳረገ ኢትዮጵያ ጠል ሃይል ነው” ብለዋል።
ኢሕአፓ ከደርግ ጋር ብቻ ሳይሆን ከጥንስሱ ጀምሮ ጸረ ኢትዮጵያ የሆነውን የወያኔ ቡድን ሲታገል መቆየቱን ገልጸው፤ ዛሬም የድርጅቱ አባላት በዲፕሎማሲና በወታደራዊ መስኩ የራሳቸውን ሚና እየተወጡ ይገኛሉ ብለዋል።
ይህ ቡድን አሁን ላይ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ለማጥፋት በሁሉም አቅጣጫ ጥቃት ከፍቶ ጭፍጨፋ እያደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህን ተከትሎ የፌዴራልና የአማራ ክልል መንግስታት ያደረጉትን ወቅታዊ ጥሪ ፓርቲው እንደሚደግፍ አረጋግጠዋል።
“የአሸባሪው ቡድን የጥፋት ተግባር በየቤታችን እስኪደርሰ መጠበቅ የለብንም” ያሉት መጋቢ ብሉይ አብርሃም፥ ጉዳዩ በየትኛውም ቦታ እና ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ የሚመለከት የህልውና ጥያቄ መሆኑን አጽንኦት ነው የገለጹት።
“በዚህ ህልውና ዘመቻ ውስጥ የማይሳተፍ ኢትዮጵያዊ ሊኖር አይገባም” ነው ያሉት።
በመሆኑም “ኢትዮጵያውያን በአንድነት ቆመን እየተከፈለ ያለውን መስዕዋትነት ማጠናከር ይገባል” ብለዋል።
ህብረተሰቡ ተደራጅቶ ያለማንም ቀስቃሽ እስካሁን ዋጋ ማከፈሉን ገልጸው፤ ህብረተሰቡ በየትኛውም ሕጋዊ አደረጃጀት በመደራጀት ለራሱ እና ለአገሩ ጠበቃ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
25
Engagements
–
Distribution Score
Boost Post
20
4 Comments
1 Share
Like
Comment
Share