አሸባሪውን ቡድን በአጭር ጊዜ ለመደምሰስ እንደህዝብ መዝመት እንደሚገባ የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ህልውናን ለማስከበር ማንኛውም ጤናማ ሰው በህዝባዊ ማዕበሉ መሳተፍ አለበት ሲሉ የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ያለዓለም ፈንታሁን ተናገሩ።
የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር አሸባሪው ሕወሓት እያደረሰ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
የመግለጫው ሙሉቃ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
አሸባሪውን ቡድን ከሰሜን ጎንደር ዞን አስወግዶ ለመቅበር፣ ሠላምን ለማረጋገጥና ሀገርን ከመፍረስም ለመታደግ እየሰራ ነው፡፡
የሰሜን ጎንደር ህዝብ ከመቸውም ጊዜ በላይ በህዝባዊ ማዕበል የመጣውን ጠላት በህዝባዊ ማዕበል ለመቀልበስ የተሰራ ነው፤ ጠላት በተገቢው መንገድ እንዲመታ አደረጃጀቱም በተሻለ መንገድ እየተጠናከረ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ወቅት ለሀገር ሰላምና ለህዝብ ደህንነት የዕለት ከዕለት ስጋት እየሆነ የመጣውን ወራሪና አሸባሪ ቡድን ከመመከት ባለፈ÷ በአጭር ጊዜ ለመደምሰስ የወጣቱ ተነሳሽነት፣ የህዝቡ እንቅስቃሴ በከተሞችና በገጠር በጣም አነቃቂ በመሆኑ ጠላት የመጣው በህዝባዊ ማዕበል በመሆኑ በዞኑ በኩልም ህዝባዊ ንቅናቄ የሚደረግበት ወቅት ነው።
የሰሜን ጎንደር ዞን ከሌሎች ዞኖች በላይ ሰፊ የህዝብ ማዕበል የሚያስፈልገው በመሆኑ÷ በትኩረት እየተሰራበት ይገኛል፡፡
እንደ ህዝብ በንቅናቄ የወጣውን ማዕበል መሪ ተዘጋጅቶለት ጠላትን ለመዋጋት በሚችለው መንገድ ዝጁ ነው፡፡
ቀሪው የአካባቢው ህዝብም÷ ሰርጎ ገቦችን ከመቸውም ጊዜ በላይ ነቅቶ በመጠበቅ ለተጀመረው ትግል ስኬታማነት በልዩ ትኩረት ለመስራት ዝግጁ ናቸው፡፡
መዋጋት ይችላል የሚባለው ሰው በሙሉ ስነ-ልቡናው ከፍ ያለ መሆኑን ያመላከተው መግለጫው÷ ህዝቡ ይደራጃል፤ ይመራል፤ በድል ይመለሳልም ብሏል።
ሰርጎ ገቦችን ለመከላከሏ የህዝብ ንቅናቄ ተደርጎ ከተሞችን በንቃት ሊጠብቁ የሚችሉ አደረጃጀቶች እየተፈጠረ ነው። ኬላዎችም በተጠናከረ መንገድ ይጠበቃሉ፤ በዚህ ጦርነት ጏላፊነት የማይወስድ አይኖርም ብሏል መግለጫው፡፡
የአሁኑ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ጠላትን አይገቡ ገብቶ ማጥፋት የሚያስችል ቁርጠኝነት ተይዞ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በዞን፣ በወረዳና በከተማ ደረጃ ያሉ አመራሮች ከፊት ሆነው ንቅናቄውን ይመሩታል መባሉን ከዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!