Fana: At a Speed of Life!

የሱማሌ ክልል ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን ድንበር በንቃት እንደሚጠብቅ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ የመሩት የሱማሌ ክልል የፀጥታ ኮሚቴ ሳምንታዊውን ስብሰባ አካሂዷል።

በመድረኩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የፀጥታ አካላት የተገኙ ሲሆን÷ በወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎ አራት ነጥቦችን በማውጣት ተጠናቋል።

በዚህም ክልሉ ለወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን ትኩረት በመስጠት የክልሉን ውስጣዊ ሰላምና ፀጥታ ማጠናከር ላይ መሰራት እንዳለበት ተቀምጧል።

በተጨማሪም ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን ድንበር በንቃት መጠበቅና ሽብርተኛ ቡድኖች ወደ ክልሉ እንዳይገቡ መከላከል ላይ እንደሚሰራ ተገልጿል።

የብሄር ግጭቶችን የሚያነሱ አካላት መከላከልም የክልሉ የትኩረት አቅጣጫ እንዲሆን በውይይቱ መለየቱን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.