Fana: At a Speed of Life!

የክተት ጥሪውን ለመቀላቀል ቁርጠኛ መሆናቸውን የባህር ዳር ነዋሪዎች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመንግስት የተላለፈውን የክተት ጥሪ ተቀብለን የህልውና ዘመቻውን ፈጥነን ለመቀላቀል ቁርጠኛ ነን ሲሉ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
በየአካባቢው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት የህዝቡን ልብ የሚሰልቡ ቅጥረኞችን ተከታትሎ ለህግ ማቅረብ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
አሸባሪው ህወሓት እየፈፀመ ያለውን ወረራ ለመቀልበስ የመንግስትን የክተት ጥሪ ተቀብለው ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን የባህርዳሩ ነዋሪ አቶ አበባው አማረ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
የወራሪው የጥፋት ተግባር የሚጎዳው አማራን ብቻ ባለመሆኑ÷ ሀገርን ከገጠማት ውስብስብ አደጋ ለመታደግ መላ ኢትዮጵያዊያን በጋራ ተነስተው አሸባሪውን መደምሰስና የኢትዮጵያን የቀደመ ነፃነት ማረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
በመሆኑ በጥሪው መሰረት ሁሉም ዜጋ ‹‹ሀገሬን ከወራሪው ኃይል መታደግ አለብኝ ብሎ›› ማሰብና በመዘጋጀት የድርሻዉን ሊወጣ እንደሚገም አሳስበዋል፡፡
ህወሓት የአማራን ስነ-ልቦና ለመስለብና ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከታዳጊ ህጻናት እስከ ሽማግሌ አሰልፎ እየፈፀመ ያለውን ወረራ መመከት የምንችለው÷ እኛም ለአካባቢያችንና ለሀገራችን ዘብ ስንቆም እና መንግስትም ለጠራው የክተት ጥሪ ግንባር ቀደም ሆኖ በማደራጀትና በማስታጠቅ በቁርጠኝነት ሲመራ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
የክተት ጥሪውን በመቀበል የጥፋት ቡድኑን ለመፋለምና ለሀገሬ ክብር ስል እስከህይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ም ቁርጠኛ ነኝ ነው ያሉት፡፡
የዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት የነርሲንግ ተማሪ የሆነው ወጣት ዘላለም ውበት በበኩሉ፤ መማርም ሆነ ሰርቶ መኖር የሚቻለው ሀገር ሰላም ሲሆን መሆኑን ገልጾ÷ አሸባሪውን ቡድን ፊት ለፊት ገጥሞ ማሸነፍ እንጂ በሚያሰራጨው የሀሰት መረጃ በስነልቦና ተሸናፊ መሆን እንደማይገባ ተናግሯል።
ህልውናችንን የምናረጋግጠው የክተት ጥሪውን ተቀብለን የበኩላችንን ስንወጣ ነው፤ እኔም ሀገር እንድትድን የህልውና ዘመቻውን በመቀላቀል አሸባሪውን ቡድን ለመፋለም ቁርጠኛ ነኝ ነዉ ያለዉ፡፡
በየአካባቢው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት የህዝቡን ልብ የሚሰልቡ ቅጥረኞችን በተለይ ወጣቱ ተከታትሎ ለህግ እንዲያቀርብም መልዕክት አስተላልፏል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.