Fana: At a Speed of Life!

ለኢትዮጵያ ህልውና ሕይወታችንን ለመክፈል ዝግጁነን አሉ ወጣቶች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር የማዳን ጉዳይ የተወሰነ አካል ባለመሆኑ ሁሉም ዜጋ ሀገርን ማዳንና አሸባሪው ህውሃት ለማጥፋት መነሳት አለበት ሲሉ የሀረሪ ክልል ወጣቶች ገልጸዋል፡፡
ሀገር ከሁሉም ይቀድማል በመሆኑም ሁሉም ዜጋ በተለይም ወጣቱ ሀገሩን ለማዳን መዘጋጀትና የአካባቢውን ሰላም መጠበቅ እንዳለበትም ነው ወጣቶቹ ያሳሰቡት፡፡
አሸባሪው ህውሓት የመላው ኢትዮጵያውያን ጠላት ነው፤ በመሆኑም ሁሉም ዜጋ የሀገሪቱን ጠላት ለመመከት መዘጋጀት ይገባልም ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከዚህ ቀደም ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም በመለገስና የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ድጋፍ ማድረጋቸውን የጠቆሙት ወጣቶቹ÷ አሁንም ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሳውን ቡድን ለመደምሰስ እስከ ግንባር ለመዝመትና ሀገራቸውን ለመታደግ ዝግጁ መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.