የድሬዳዋ ነዋሪዎች የህወሓትን ሴራ በማጋለጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የሕወሓት ቡድን እኔ ያልመራኋት ኢትዮጵያ መበታተን አለባት ብሎ የቁም ቅዠቱን ለመተግበር የትግራይን ወጣቶች አታሎ በኢትዮጵያ ላይ እያዘመተ ለትውልዱ ሳይራራ እየማገዳቸው መሆኑን የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢብራሂም ዩሱፍ ገለጹ፡፡
ይህ ሰይጣናዊ ባህሪን የተላበሰው አሸባሪ ቡድን÷ በደረሰባቸው ቦታዎች ሁሉ ንፁሃንን በግፍ እየረሸነ፣ እያረደና እያቃጠለ ክፋቱንና አሸባሪነቱን በአደባባይ እያረጋገጠ ነውም ብለዋል፡፡
በመሆኑም ኢትዮጵያ ከየትኛውም አቅጣጫ ለመጣ ወራሪ ኃይል እጅ ሰጥታ የማታውቅ ልጆቿ ታፍራና ተከብራ የኖረች ሃገር መሆኗ አስታውሰው÷ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይሉ፣ ሚሊሻውና መላው የሀገራችን ህዝብ ከዳር እስከዳር ተነስተው ይህን ወራሪና አሸባሪ ቡድን ለመደምሰስ ብርቱ ትግል ሊያደርጉ እንደሚገም አሳስበዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ የፈፀመብንን ወረራና የተደቀነብንን ሃገር የማፍረስ አደጋ ለመቀልበስ÷ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም የሞራልና የሎጂስቲክ ድጋፍ በማድረግ፣ በግንባር በመዝመት የአሸባሪ ቡድኑ ተላላኪዎችን በማጋለጥ፣ አሳልፎ በመስጠት እና የተፈናቀሉ ዜጎችን በመደገፍ መላው የድሬዳዋ ነዋሪዎች የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላፈዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!