አመራሩና ህዝቡ ሙሉ አቅሙን ኢትዮጵያን ማዳን ላይ ማድረግ አለበት-የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ በወቅታዊ ክልላዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚያግዙትን የውጭ ጠላቶችና የውስጥ ተላላኪዎቹን አስተባብሮ በሁሉም አቅጣጫ ውጊያ ከፍቶብናል።
በሀገር ላይ የተቃጣውን አደጋ ለመመከትም ህዝብና መንግስት ሰፊ ርብርብ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
በሀረሪ ክልልም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና ነዋሪው በተለያየ መልኩ በቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ነው የገለጹት።
በቀጣይም አመራሩና ህዝቡ የህልውና ጦርነቱን ውስብስብ ባህሪ በመገንዘብ ሙሉ ትኩረቱንና አቅሙን ኢትዮጵያን በማዳንና የክልሉን ሰላም በማስጠበቅ ላይ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የተደቀነብንን ሀገር የማፍረስ አደጋ ለመቀልበስ ሁሉም አመራር ተቀናጅቶ ፣ ተናቦ እና የተግባር አንድነት ፈጥሮ ሀገርን ከብተና ክፉ ምኞት መታደግ እንዳለበት ገልጸዋል፡፡
መላው የክልሉ ነዋሪዎች እና የፓርቲው አባላትም የሀገር መከላከያ ሰራዊትን እና ሌሎች የጸጥታ አካላትን በሞራል እና በሎጅስቲክስ የመደገፍ ተግባሩን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑንም አንስተዋል።
ወጣቶችም እንደከዚህ ቀደሙ የመከላከያ ሰራዊቱን በመቀላቀል መስዋዕትነት የተከፈለበትን ሀገር እንዲያስቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያን ከማፍረስ ሰይጣናዊ ሕልማቸው ጋር አብሮ ለመቅበር ከመቼውም በላይ አንድነትን በማጠናከር ከጀግናው የመከላከያ እና ሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጎን መቆም እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ህዝብን ባሳተፈ መልኩ የአሸባሪውን ተላላኪዎች በተደራጀ መንገድ በማጋለጥ የአካባቢን ሰላም ከማስጠበቅ ጎን ለጎንም በጦርነቱ የተፈናቀሉ ዜጎችን መደገፍ እንዲሁም እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን በትኩረት መስራት እንደሚገባም አቶ አብዱጀባር አስገንዝበዋል።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ዛሬም በየግንባሩ በጽናትና በጀግንነት እየተፋለሙ ለሚገኙት የመከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የጸጥታ ሃይሎች ጠንካራ ደጀን ከመሆን ባሻገር አመራሩንና ህዝቡን በማስተባበር በግንባር በመሰለፍ ሁሉንም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!