Fana: At a Speed of Life!

የግል መሳሪያ ያላቸው ነዋሪዎች በሁለት ቀን ውስጥ እንዲያስመዘግቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሳሰበ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ከዚህ ቀደም መሳሪያ ያስመዘገቡም ሆነ ያላስመዘገቡ የግል መሳሪያ ያላቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በሁለቱ ቀናት ውስጥ እንዲያስመዘግቡ የከተማ አስተዳደሩ የሰላምና ደህንነት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ አሳሰቡ።
ሃላፊው አዲስ አበባ ውስጥ የሚኖር ማንኛውም ነዋሪ በእጁ የሚገኙ መሳሪያዎችን “ከዚህ ቀደም ያስመዘገበም ሆነ ያላስመዘገበ ” ዛሬን ጨምሮ በሁለት ቀን ዉስጥ በአቅራቢያው በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች እንዲያስመዘግብ ጠይቀዋል።
የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ ወቅታዊ ፀጥታን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በመንደር እርስ በርስ ተደራጅቶ የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።
አደረጃጀቱም ከፀጥታ ተቋማት ጋር እየተናበበ አካባቢውን መቆጣጠር እንዳለበትም ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ፀጥታ ሰላም ቢሆንም ውዥንብር የሚፈጥሩ አካላት በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው ብለዋል።
የፖሊስና የመከላከያ ፀጥታ አካላት ከኦሮሚያ ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ሰላምና ደህንነት ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የጦር መሳሪያን በተመለከተ በህግ የተመዘገበም ይሁን ያልተመዘገቡ አካላት በሁለት ቀናት ማስገንዘብ አለባቸው ብለዋል።
የጦር መሳሪያው በመንግስት ከታወቀና ህጋዊ ከሆነ በራሱ የአካባቢውን ፀጥታ እንዲያስጠብቁ ይደረጋል ብለዋል።
መሳሪያ ያላቸው አካላት አካባቢያቸውን መጠበቅ የማይችሉ ከሆነ ለቅርብ ሰው ወይም ለመንግሥት በአደራ ሰጥተው እንዲጠበቅበት ይደረጋል ብለዋል።
ነዋሪዎች አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ሰርጎ ገቦችን ለመቆጣጠር የሚፈጸሙ መደበኛና ድንገተኛ ፍተሻዎችን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።
የመኖሪያ ቤት አከራዮች፣ ሆቴሎችና ሁሉም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማንኛውንም አገልግሎት ሲሰጡ ተገልጋዮቻቸውን በቅርበት እንዲከታተሉና መታወቂያ እንዲጠይቁም ሃላፊው አሳስበዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person and sitting
36,191
People reached
2,641
Engagements

-1.6x Lower

Distribution Score
Boost Post
901
84 Comments
67 Shares
Like

 

Comment
Share
May be an image of 1 person and sitting
0
People reached
17
Engagements
Distribution Score
Boost Post
14
2 Comments
1 Share
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.