Fana: At a Speed of Life!

አብሮ ለመሥራት ያሉንን ዕሴቶች ተጠቅመን አገራችንን እናሳድግ – ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያውያን አብሮ ለመሥራት ያሉንን ዕሴቶች ተጠቅመን አገራችንን በጋራ እናሳድግ ሲሉ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ጥሪ አቀረቡ፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል÷ የውይይቱ ዓላማ ብቁ የሆነ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የሰው ኃይል ለማፍራት ፣ የሠራተኛውን መብት የጠበቀ ጤናማ የአሠሪዎች እና የሠራተኞች ግንኙነት ለመፍጠር አዲስ ከተቋቋመው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ጋር በጋራ መሥራት የሚቻልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን አብሮ ለመሥራትም ሆነ አብሮ ለመኖር የታደልን በመሆናችን ያሉንን ብዙ ዕሴቶች ተጠቅመን አገራችንን በጋራ እናሳድግ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን÷ ስለ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ገለፃ አድርገው÷ ቀደም ሲል ይገጥሙ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት እና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን ለማካትት ሁሉም የበኩሉን አስተዋፃኦ ማበርከት እንደሚገባው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአሠሪና ሠራተኛ እንዲሁም ሆቴል እና ቱሪዝም ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች ላይ ጥያቄና አስተያየት ቀርቦ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ተወያዮቹ በጋራ ለመሥራት ዝግጁ እንደሆኑ መግለፃቸውን ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.